በፌደራሊዝም 15 አመት አስተዳድሮ ስርዓቱን ለአለም ያስተዋወቁ ኢማም ኢማም አህመድ ናቸው!
የሰሜኑ በአፄዎች የሚመራ ክርስትያናዊ መንግስት እና በምስራቁ በሱልጣኔት/በአሚርነት/በኢማምነት የሚመራው እስላማዊ መንግስት አንዱ በአንዱ ስር ለማስገባት፣ እምነትና ግዛት ለማስፋፋት፣ ወይም ግዛቱና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ እንዳንዴ ሃይለኛ ጦርነት በሚደረግበት፣ እንዳንዴ ጦርንቱ ረገብ የሚለበት፣ አንዳንዴም ሰላም የሚሆንበት ሁኔታዎች 800 አመታት በላይ ቆይቷል።
በእነዚህ 800 አመታት በላይ በርካታ ጦርነቶች ቢደረግም በሰሜኑን በአፄዎች የሚመራ መንግስት የምስራቁ ሱልጣኔት/አሚር/በኢማም የሚመራው እስላማዊ መንግስት በማሸነፍ እስላማዊ ግዛቶች ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር የዋለው በአፄ ሚኒልክ ዘመን 1887 ዓ/ም ነው። የምስራቁ ሱልጣኔት/አሚር/በኢማም የሚመራው እስላማዊ መንግስት የሰሜኖችን አፄዎች በማሸነፍ የክሪስቲያኖችን ግዛቶች ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር የተደረገው በኢማም አህመድ ኢብራሂም በ1530 ዎቹ ጊዜ ነበር። በእነዚህ ጊዜያት ውጭ በሁለቱም ወገኖች አንዱ አንዱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ያዋለበት ጊዜ አልነበረም። ይህ ደግሞ የሚያመለክተው ሁለቱም ወገኖች በሚያስተዳድሩት ግዛቶች በየ ራሳቸው ነፃ መንግስታት እንደነበሩ ነው። ለሰሜኑ ገዢዎች የስልጣን ማዕከላዊ ከተማ በዋናነትና በተደጋጋሚ ጎንደር እንደነበርች፣ ለምስራቁ ገዢዎች በዋናነት ሐረር እንደነበረች ይታወቃል። የምስራቁ ሱልጣኔት/አሚር/በኢማም የሚመራው ግዛቶች እና ሐረርጌና ሐረር ከተማ በአፄ ሚኒልክ 1887 አሚር አብዱላሂን ከማሽነፉ በፊት አንዴም በሰሜኑ አፄዎች ቁጥጥር ስር ገብተው አያውቅም።
ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ መሰረቱ ግሪኮች ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት በውል ከታወቀችው ከግብፅ በስተደቡብ የሚገኘው የአፍሪቃ ክፍል የሚጠራበት አጠቃላይ ስያሜ እንደነበር የታሪክ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ሆኖም ግን በግዛት ወሰን ግን የትኞችን አካባቢ እንደሚያከትት ግልፅ የሆነ ነገር የለም። ስለዚህም በዚህ በኢትዮጵያ ስም የሰሜኑ በአፄዎች በርካታ ነፃ የሆኑ እና በራሳች ማስተዳደር ግዛት ውስጥ ያልነበሩ በምስራቁ በሱልጣኔት/በአሚርነት/በኢማምነት ይመሩ የነበሩ ግዛቶችንም ጭምር የራሳቸው አድረገው ይናገሩ እንደነበር ነው። ዳሩ ግን ከላይ እንደተጠቀሰው በአፄ ሚኒልክ 1887 በፊት በምስራቁ በሱልጣኔት/በአሚርነት/በኢማምነት ይመሩ የነበሩ ግዛቶች እንዳች ጊዜም ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ስር ውለው የተዳደሩበት ዘመን አልነበረም።
ኢማም አህመድ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የተነሳው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1508 ዓ/ም ነው።
ለኢትዮጵያ አንድነት ከሰፊ ሀገር ግዛት ጋር ለማቋቋም ከማንኛውም አፄዎች በተሻለ ሁኔታ ለመመስረት የሞከረው ኢማም አህመድ ኢብራሂም አልጋዚ ነበር። የአሁኗ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራን፣ ሱዳን ኑባያ ግዛት፣ ብሪትሽ ሶማሌ ላንድን፣ ኢታሊ ሶማሌ ላንድን እና ፍሬንች ሶማሌ ላንድ(የአሁና ጁቡቲ) በማጠቃለል በአንድ ሀገር ጥላ ስር ለአስራ አምስት አመታት 1520-1535 ዓ/ም አስተዳድሯል። በዚያን አስተዳደር ዘመን በtraditional ፌደራል ሲስተም ሁሉም አካባቢያቸው ራሰቸው በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በመፍቀድ በማዕከላዊነት መንግስት በኢማሙ ስር ይገዙ እንደነበር ይታወቃል።
ከኢማም አህመድ አገዛዝ በፊት የዜይላ ግዛቶች ወይም የምስራቁ በሱልጣኔት/በአሚርነት/በኢማምነት ይመሩ የነበሩ ግዛቶች በአፄዎች ቁጥጥር ሙሉ በሙሉ ስር የዋለበት ጊዜ የለም።
ከኢማም አህመድ በፊትም ሆነ በኃላ በሰሜኑ በአፄዎች ስር የሐረርጌ ግዛት በፍፅም እንዳልወደቀች ነው። የኢማም አህመድን ወረራ መፅሐፍ የሐረርጌ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና እንደተዋሀደች የሚገለፀውን ክፍል ፅሑፍ ስናይ ከኢማም አህመድ በፊት ኢትዮጵያ አካል እንደነበረችና ከዚያ በኃላ እንዳልነበረች ሆኖም ግን በሚኒልክ ዘመን ከኢትዮጵያ ጋር እንደተዋሀደች ነው የሚያመለክተው።
ኢማም አህመድን ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ የገዛበትና የሞተበት ጊዜ እና ሚኒሊክ ሐረርጌን የተቋጣጠረበት ዘመን ሲታይ የ352 አመታት ልዩነት አለ። ይህ የሚያመለክተው ሌሎች የምስራቅ ኢስላማዊ ግዛት ትተን ሐረርጌ ብቻ ከኢማም አህመድ ሞት እና ሚኒልክ ሐረርጌን የተቆጣጠርበት ጊዜ አንፃር 352 አመታት ሐረርጌ ነፃ መንግስት እንደነበራት ያመለክታል።
የዜይላዕ ግዛቶች ወይም የምስራቁ በሱልጣኔት/በአሚርነት/በኢማምነት ይመሩ የነበሩ ግዛቶች ከኢማም አህመድ በፊት በአፄዎች ስር ይተዳደሩ እንዳልነበረ ግን ኢትዮጵያ በሚል ሰፊ ግዛት ስያሜ የራሳቸው ግዛት አድርጎ የመቆጠር አዝማሚያ በስፋት ነበር። እነዚህንም ግዛቶችን ግን ለመቆጣጣር በርካታ ጥረትና ጦርነቶች በየጊዜው ተደርጓል። ሆኖም ግን ሳይሳካላቸውም ቀርቷል። የዛይላ ግዛቶች ወይም የምስራቁ በሱልጣኔት/በአሚርነት/በኢማምነት ይመሩ የነበሩ ግዛቶች በተለይም ሐረርጌና ከተማዋ ሐረር(በግብፅና ቱርክ ቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ በሰተቀር) ራሷን የቻለች ነፃ መንግስት እንደነበረች ሉአላዊነቷን ያጣቺው ከሺህ አመታት በኃላ በአፄ ሚኒልክ ዘመን እነደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያመለክታል።
በቅኝ ገዢዎች የተከፋፈለውም የአከባቢዎ ግዛቶችም የራሱ ተፅእኖ እንደነበረውም መዘንጋት የለበትም።
የታሪክ ማጅራት መቺዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የመበራከታቸው ምክንያት የኛ ዝምታ ነው ከማለት ውጪ ምን ይባላል?
እውነት ትቅጠን እንጂ አትበጠስም!
~•~
ኢትዮጵያዊ ታሪክ ወግ ተረት ጥረቃው
የታሪክ እንግድድ የእብለት አተላው
በጭፍን ጥላቻ በነ ትምክህት ኩራት
በሚል አፋኝ ህጎች እኔን ስማኝ እብደት
ሃገሬ ጠቁራለች ከስላለች ፍማለች በእንቶፈንቶ ውሸት
በውሸት ታሪኪታ ሐገርን ታፈርስ እንጂ ከቶ ትገነባት
በታሪክ እንግድድ የሓሊት እስሮች ክብሯ ተዘልዝሎ
በዳዩ ሲሞገስ ሲሸለም ሲቀባ ጎሽ ልጄ ተብሎ
ታሪክ ነፍሯል ያኔ በጥቅም ባደሩ ሆድ አደር ብእረኞች
እውነት ሰሚን አጥታ በግፍ ዱላ ፍዳ ስቃይዋን በልታለች
.
.
.
.
.
ይገርማል.
.
ያን ጀግና ብርቱ ሰው አህመድን ሲያጥላላው
የሃበሻ ግብዝ የምሁር ክምችት የታሪክ ገለባው
ከዚህ ወዲያ ማዶ ከእውነታው ማማ
ከሙስሊሙ ቀዬ ከታሪክ ሁነቱ ከከፍታው ግርማ
ባቲ ድል ወንበሯ የእርሷ ያረገችው የወንዶች አለቃው
የኩፍርን ወራሪ በሰይፉ ስንዘራ አሳሩን ያበላው
ከሃበሽ ነበረ ከኛው ወገን ስጋ አላህ የኸለቀው
ማንም ምንም ቢለው በፍትህ የገዛ አስራ ቤት ሃበሻን
እብለትን ተፋልሞ እውነት ያነገሰ ላገሩ ፍጡራን
ኢማሙ አህመዱ ፀረ ክፋት ክስተት
የአፄን ጥጋብ ቋጪ የጠላቱ መቅሰፍት
ያያቴን ጀግንነት ደብቀው አብየው አድበስብሰውታል
ያልነበረን እውነት በዋሾ ቀለማት በዕምነት ልዩነት ክደው ፅፈውታል
በጭፍን ፀሀፍት የጀግኖቼ ገድል በብዕር ተቀልቷል፣
የኢማሜን እውነት ሽንብራ ኩሬ ላይ በድል መቀናጀት፣
ሽንብራ እየቃሙ ለሆዳቸው አድረው እውነትን አረዱት ፣
የአህመድን ጀግንነት ያለእማኝ ደበቁት
ለታሪክ መዛግብት ለአፄው መሸነፍ ማደነጋገሪያ
እውነት ተውንጅላ በጊዜ ታፍና ወርዳለች ዘብጥያ
ታሪክ በጨቋኞች ታፍና ታማለች
ነገን ነፃ ሆና በብዕር ዋስትና ዳግም ታብባለች
.
ላ’ንተ ግን እርማት
.
.
.
አለም ሳትመሽብህ ባለጊዜ ሁነህ ታሪኬን የሰረዝክ፣
ዛሬን አላውቅ መስሎህ እውነት አሳምማህ ሀሰትን የሰበክ፣
ልታክመኝ መጥተህ ሳላክምህ አትሂድ፣
መድሃኒቱን እንካ እኔ አቃለሁ እያልክ በ’ሳት አትማገድ፣
የባለድልን ዘውድ ካነሳህበት ራስ ይሻላል ብትመልስ፣
ምንም መሪር ብትሆን እውነትን ተጋታት ድልን ላሸናፊው ለሚገባው መልስ።