ትሻልን ትቼ ትብስን
~•~
የኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ፣ አዲሱ የኢትዮጵያ የፌድራል ስርዓት አወቃቀርና አከላለል ስሌትና ቀመር ምን የተለየ ነገር ይዞ ይሁን?
ሰሞኑን የብልፅግና ፓርቲ አላማው ዙሪያ የፌድራል መንግስት እና ከትግራይ ክልል በስተቀር የሁሉም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህ ስልጠና መረሀግብር ከመወያያ ርዕስ ጉዳዮች አንዱ ”የፖለቲካ ብልፅግና የማረጋገጥ ትልምና ፈተናዎች” የሚል ርዕስ ያለው ሰነድ ነው። ሰነዱ የአገሪቱ የፌድራል ስርዓት አወቃቀርና አከላለል ችግሮችን ይዳስሳል፣ የመፍትሄ ሃሳብ ይዞ ብቅ ብሏል።
የስልጠና ሰነዱ የፌድራል ስርዓት አከላለል በተለይም በማንነት ላይ የተመሰረተ የፌድራል ስርዓት ውስጥ በአንድ ክልል ሌሎች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በብዛት የሚገኙበት አከባቢ አጠቃሎ መከለሉ እንደ ችግር አስቀምጧል። ሌላው ጉዳይ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 39 ያለ ገደብ የመገንጠል መብት ለብሔሮች ብሐረሰቦች እና ህዝቦች መሰጠቱ ከፌድራል ስርዓት ይልቅ ወደ ኮንቬድሬሽን ያደላ ነው የሚል ትችት ይዛል።
ለዚህም ችግሮች መፍቲሄ ተብሎ የታሰበው የህገ መንግስቱ ሰነድ በአዲስ መከለስ፣ አከላሎችንና አስተዳደሮች ማሻሻል እንድምታ ያለው ነው።
የክልሎች አመሰራረት ሰነዱ ታሳቢ መደረግ አለበት ብሎ የሚያቀርበው መፍትሄ፣ አንድ ክልል በአብላጫነት ብዛት ባለው ብሔር/ህዝብ መሰረት መካለል ወይም አስተዳደሩ መያዝ እንዳለበት ታሳቢ ያድርጋል።
በዚህ አከላለል ወይም አስተዳደር ውስጥ ያሉ አናሳ ማህበረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር በንዑሳን አስተዳደር እርከን(በወረዳ ወይም በቀበሌ ደረጃ) እድል እንዲሰጣቸው መደረግ እንዳለበት ያትታል።
በዚህ እሳቤ የተወሰኑ ክልሎች የሚያፈርስ ወይም አስተዳደሩን በሌሎች እንዲያዝ የሚገብዝ መሆኑ ጥርጥር የለውም። የፌድራል ስርዓቱ በማንነት ሳይሆን በህዝብ ብዛት አብላጫ ማንነት ያላቸው ህዝቦች በፌድራልም በክልልም ማስተዳደር እንዳለባቸው የሚጋብዝ አማራጭ ነው። የዚህ መለኪያ ስሌት የሚወሰደው አሁን ባለው የህዝብ ቆጠራ መነሻነትና አሰፋፈርን መነሻ ያደረገ እንደሚሆን ይገመታል። በብሔር ማንነትና ታሪክ መሰረት የተዋቀሩ የተወሰኑ ክልሎች ክልልነታቸውን በማጣት ወደ አከባቢ አስተዳደርነት የሚቀይር ይሆናል። በዚህ ስሌትና ቀመር በታሪክ አጋጣሚ በአከባቢያቸው በሌሎች መብዛት የተዋጡ የህዳጣን( አናሳ) የህብረተሰብ ክፍሎች የማንነት ማስተዳደር መብት፣ የባሰ የመዋጥና የማንነት ማጣት እድሉ ሰፌና የከፋ እንደሚሆን ይገመታል።
በታሰበው ስሌትና ቀመር መነሻነት እያንዳንዱን ክልል ምን አይነት እጣ ፋንታና እድል እንደሚገጥማቸው፣ የትኛው ማህበረሰብ እንደሚጠቅም፣ ይትኛውን እንደሚጎዳ እና ምን አይነት ውጤቶች እንደሚያስከትል መገመት ይቻላል።
በአሁኑ ጊዜ ያሉትን ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በታሰበው ስሌትና ቀመር በማስላት እያንዳንድ ክልልና ከተማ አስተዳደር በመመርመርና በመዘርዘር ውጤቱና እጣፋንታቸውን መለየትና ውጤታቸው መናገር ይቻላል።
የእያንዳንዱ ክልሎች እጣ ፋንታ ማንኛውም የሚመለከተው ሰው ወይም አካል መንዝሮ እንዲያየው እየገበዝኩኝ በጥቅሉ የሚያስከትለው ውጤት ግን በጥቅሉ የሚከተሉት ይመስላል።
በጥቅሉ በዚህ ቀመርና ስሌት አራት ክልሎችን እንደሚፈርሱ ወይም የማስተዳደር ሚናቸው እንደሚያሳጣቸው እርግጠኛ መሆን ቢቻልም በርካታ አወዛጋቢና ውስብስብነት ጉዳዮች የሚያስከትሉ ናቸው። አንዳንድ አከባቢዎች ወደ የትኛ ይጠቃለሉ የሚለው የመግባባት ስምምነት የማይገኝላቸው ሊሆን እንደማይችል፣ የሁለት ከተማ አስተዳደሮች እጣ ፋንታ እና የባለቤትናት ጥያቄዎች እና ሌሎች የውስጥ አከላለሎች በርካታ አዳዲስ ጥያቄዎችና ችግሮች ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ይገመታል። አብዛኛው የኢትዮጵያ የህዳጣን(አናሳዎች) መብት በአብዛኛው ማንነቶች እንደሚወጡና የማስተዳደር ሚናቸውን እንደሚያጡ ይገመታል።
አዲስ የብልፅግና ፓርቲ የክልሎች አመሰራረት፣ አከላለል እና አስተዳደር በአዲስ መልኩ ለማወቀር ታሳቢ አድርጎ በጅምሩ ይህን ሃሳብ ወጥኖ ብቅ ብሏል። ይሳካለት ይሁን? ወደፊት የምናየው ይሆናል። የብልፅግና ፓርቲ የተቀላቀሉ አጋሮችስ ምን ይሉ ይሁን?
ምንጭ ☞ ስውሩ ደንበኛችን