ኤልሳ የማታውቀው ህግና ኤልሳን የሚያውቃት ህግ ትውውቅ
~•~
በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ኤልሳ ከበደ የሐረሪን ህዝብ እንደህዝብ በአደባባይ የናቀ፣ የደፈረ፣ ያንቋሸሸ፣ ያወረደ፣ በህዝብ ላይ ህዝብ ያነሳሳ፣ የዘር ጥላቻ የሰበከ፣ ህዝብ የወነጀለ ሰውም ሆነ ስርዓት አልተገኘም።
ዴሞክራሲና ሃሳብን በነፃ የመግልፅ መብት ምክንያት በማድረግ ለከትና ገደብ እንደሌላው መብት፣ እንደ ኤልሳ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠር ጥቃት ጋባዥ ስም ማጥፋት የዘመተና ያዘመተ፣ የቀሰቀሰ፣ ያነሳሰና እንደ ጭቃ ጅራፍ የጋለበበት እና እርኩስ መንፈስ ያረገፈ ሰው ተይቶ አይታወቅም።
በስም ሀብሊ የሚሰደበውና የሚዘለፈው ብሔር ሀረሪ፣ በስም ኦዲፒ የሚሰደበውና የሚዘለፈው ብሔር ኦሮም፣ በእሷ በኩል የሚወደሰው በስም አንድ ብሔር ውስጡ ግፈኛና ጨቃኝ ስርዓት አድናቆት እና ተበዳይን ላይ እሾህ በቁስሉ መስደድ ወደር ያልተገኘለት አሉባልታ ቅስቀሳ ለዘመናት ስታራግብ ከርማበታለች።
እነዚህን ብሔሮች ሳያስተችኝና ሳያስወግዘኝ አያውለኝ ብላ ማሃላ ከራሷ ጋር ሴጣይታናዊ ቃል ኪዳን ገብታ የተሳሰረች ይመስላል። ለማንኛውም ፖለቲካዊ ቡራኬና ውዳሴ ማጣፈጫ የሐረሪን ብሔር፣ ክልሉና የክልልን መሪዎችና ገዢ ፓርቲዎች ስም አለአግባብ ማጥፋት የነገር ወቀጣ የተፈጠረችለት የስራ መስክ ይመስል ለእኩይ አላማ ፀንታ ቆማ ዘምታበታለች።
ክልሉን በማወቅ ቀረቤታ ስላለኝ ታማኝነትና እውነታው ላቅ ያለ ቦታ በተመልካች ዘንድ ይሰጠኛል/ይኖረኛል በሚል መተማመን በውሽት የተቀነባበረና በመርዝ የተለወሰ የዘር ጥላቻን በማንኛውም አጋጣሚና ሚዲያ ያላስተጋባችበት ቀን የለም።
በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያ በፌስቡክ በራሷ ስም እና ስለ ሐረር ዝም አንልም በሚል ስያሜ ለፖለቲካ አላማዋ የከፈተቻቸው እና ስታሰራጨው የነበሩ መልዕክቶች የተመለከተ ሰው የጥላቻና ሐሰተኛ ወሬ በኢትዮጵያ የተፈቀደ የወንጀል ተግባር እና የማያስጠይቅ ድርጊት እስከሚያስመስለው ደርሷል። በሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ በአስራት፣ በኢሳትና በመሰል ሚዲያዎች ያለ ማንም ከልካይና ጠያቂ የዘር ጥላቻ እና በህዝብ ላይ ህዝብ የማነሳሰት ተግባር ስትፈፅምባቸው የነበረ አውደ ወሬ ግባአቶች ማስተላለፊያ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች ናቸው።
በሰብአዊ መብትና የሴቶች የህግ ባለሙያ ማህበር ተቋማት ሽፋን፣ ደጀንና መጠቀሚያ በማድረግ ያሻትን የህግ ጥሰት ለመፈፀምና አላማውን ለመሳካት መጠቀሚያ የተመቻቸ ዋሻም ሆኖላታል።
በሐረሪ ብሔር፣ በክልሉ መንግስት፣ ተቋማትና አመራሮች ላይ ያነጣጠረ የወንጀል ድርጊቶች ለፖለቲካ አላማ ሲትፈፅም ከርማለች። ለፖለቲካ አላማ ህዝብን ማደናገር፣ በበሬ ወለደ ወሬ ህዝብን ማሸበር፣ የሐሰት ህዝብን በህዝብ ማነሳሳት ፣ ለስንት ዘመናት አብረው ተዋልደው የሚኖሩትን ህዝብ አንዱን በዳይ ሌላውን ተበዳይ ጠባይ ያላቸው ሐሰተኛ መግለጫዎች መሰጠት፣ ስም ማጥፋትና ሐሰትኛ ሐሜት መልቀቅ፣ መልካም ስምና ክብር ማጉደፍ፣ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃና መግላጫ የመሳሰሉት ወንጀሎች በርካታ አመታት በተደጋጋሚነት በተለያዩ መብቶችና ጥቅሞች ላይ ተደራራቢ ወንጀል የሚያቋቁም ተግባራትን ስትፈፅም አደብ እንድትገዛ የመከራትና ያስጠነቀቃት አልነበረም። ይባስ ብላም በማን አለብኝነትና ንቀት ዘወትር የተፈቀደ ተግባር ይመስል በመቀጠል ለመጨረሻ ለእስር የዳረጋት ድርጊት በገዛ ስራዋ ለማይቀረው የህግ ተጠያቂነት ጊዜው ደርሳ ለማየት በቅታለች።
ኤልሳ መረን የለቀቀ የወንጀል ድርጊቶችን በአደባባይ በማን አለብኝነትና ንቅት ሲትፈፅምና የአንድን ብሔር ህልውናና ማንነት በመድፈር የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ በይፋ ስታውጅ እንደ መብት ተሟጋችና መንግስትን መተቸት አድርጎ በመውሰድ የሚከራከሩ ወገኖች እሷ
ከምታራምደው የዘር ጥላቻ ፖለቲካ በሐሳብም ወይም በአላማ የሚጋሩ ሰዎች ካልሆኑ በቀር ድርጊቶቹ በንፁህ ህሊና ለሚመዝን ሰው የተደበቀና ውስብስብ ማስረጃ የሚያስፈልገው እንዳልሆነ ማንኛውም ተራ ዜጋ ሊያረጋግጠው የሚችል ገለጭ ኩነት ናቸው።
አሁን ለእስር የዳረጋትን ድርጊት እንኳ ትተን የእስካሁኑ የዘር ጥላቻና ብሔር ላይ ብሄርን ማነሳሳት፣ ስም ማጥፋትና የህዝብን አስተሳሳብ መበረዝና ማናውጥ የፈፀመቻቸው ድርጊቶች አለመጠየቋ የሚያስተሳስብና የሚያሳዝን ቢሆንም እያንዳንዱ ድርጊቶች የተመለከተ ሰው በራሳቸው ከበቂ በላይ በህግ የሚያስጠይቁ ጉዳዮች መሆናቸው ከህግ የበላይነት አይን የተደበቁ አይደሉም ። እስከዛሬ ለናኘችበት እና ሆን ብላ ለፈፀመቺው ድርጊቶች በሙሉ በህግ ልትጠየቅ ይገባል።
በዚህ ጉዳይ ማንኛውም አካል፣ አክቲቪሲትና ሰብአዊ መብት ተሟጋች ነኝ ባይ እጁና አፉን ሊያነሳ ይገባል።ምክንያቱም የህግ ልእልና ሊከበር ይገባል!
የህግ የበላይነት ይከበር! በሰመ ዴሞክራሲና የሃሳብ ነፃናት መብት ስም ለወንጀል መሸሸጊያ መሆን የለበትም። የህዝብ ሉአላዊነትና ማንነት ሊከበር ይገባል። የህዝብ ህልውና በህገ ወጥ ግለሰብ ህልውና ሊደፈጠጥ አይገባም። በዚህ ጉዳይ መተባበር፣ በወንጀል መተባበርን ያመለክታል። የህግ የበላይነት ሲተገበር ለአጉል ትብብር ከመፈራገጥ ይልቅ በፊት ያን ሁሉ በአንድ ብሄር ላይ ስራዬ ብላ ስትዘምት ተይ! ብሎ መምከር ይቀድም ነበር ። ያን ሳታደርግ አሁን ለሷ አጉል ውሃ ወቀጣ ትብብር ዋጋ ቢስ ነው ።
ብሄር የስርአት አልበኞች መደበቂያ አይደለም። እኛ ሐረር ከተማ ላይ ከሁሉም ብሄር ጋር ተዋልደን፣ ተፋቅረን፣ ተከባብረን አንተ ትብስ ተባብለን ነው የምንኖረው። ለአንድም ብሄር ጥላቻ የለንም ። ሌላው ቢቀር የኤልሳ ሐሰት መረጃ አቀባዮች ጋርም ቢሆን እንደሷ በግልፅ በጭፋን ጥላቻ በጅምላ እልቂት ፕሮፖጋንዳ ስላልዘመቱ ከነሱጋም ቢሆን በሰላም እንኖራለን ። ብሄሯ ይሄ ስለሆነ ያ ስለሆነ የሚለው ካርድ መዛችሁ መጠቀም የምትሺ ሰዎች ካርዱ ስለማይሰራ አትልፉ።
ወንጀለኛ ብሄር ጭንብል ውስጥ ተደብቆ ህግ ይጥሳል ።ህግ ግን ብሄር የለውም ለሁሉም እኩል ነው።ማንም ስራው ያወጣዋል። ሁላችንም ህግን በማያከብሩት ማንኛውም ሰዎች የህግ የበላይነት እንዲከበር ድምፅ እናሰማ ።
አፌው ወጠኒ