እላዩ በግ ውስጡ ቶክላ፣ የሃይማኖት ካባው ሲገለጥ

እላዩ በግ ውስጡ ቶክላ፣ የሃይማኖት ካባው ሲገለጥ
ብፅወ አቡነ ማቃሪዩስ የለየለት የውሸት መግላጫ መስጠቱ ለምን አስፈለገ?
ይህ ሰው ሃይማኖታዊ አባት የሚሉት አስተሳሰብም፣ ስብዕናምና ምግባርም የለውም።
የሰውየው ምግባርና ተግባር የአንድ ፅንፈኛ ተቋም የፖሊቲካ፣ የተንኮል፣ የሸፍጥና የሽብር መሪና አማካሪ ለመሆኑ በኤርትራ የነበረ የኢትዮጵያ አማፂ በሽብር የሚፈለግ ድርጅት ድጋፍና ማነቃቂያ ሰበካ ንግግር ለማድረግ የተጓዘው ርቀት ሲታይ የሃይማኖት አባት ሳይሆን የአንድ አማፂ ድርጀት የስነ ልቦና ክፍል ኃላፊ ያስመስለዋል።
የሰውየው አደገኝነትና የፖለቲካው ተልዕኮ ከኤርትራ ጀመሮ በአማራ ክልል ወጣቶችን በማደራጀት በትግራይ ተወላጆች ላይ ግድያና ጥቃት ሲፈፀምና ሲያስፈፅም መኖሩ እስከ ሐረሩ የጥምቁቱ በአል አከባበር ችግሮች ከስተጀርባ የሴራ ውጤት ጭምብሉ ሲገለጥ፣ የንብረት ውድመት፣ የነውጥ፣ የሽብርና የዘር፣ የብሔርና እምነት ማጥፋት ሙከራ አፈፃፀም ጀርባ መኖሩ ግብሩ በግላጭ ያሳየ ነው።
ይህ ሰው ወደ ክልሉ ለምን መጣ የሚለውን የእስከ ዛሬው ድረስ ሴራውን መፈተሽ አላማውን መረዳት ብዙ መመራመር የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።
የጥምቀት በአል አከባበር ውቀት በክልሉ የተከሰቱ ችግሮች በክልሉን መንግስት ማላከክ፣ ወንጀላና ስም ማጥፈት፣ የራስ ጥፋትን መሸፋፋን ለምን አስፈለገ? በችግሮቹ ክስተት ዙሪያ ዋና ተዋናይነት ሚና መጫወቱ ለመደበቅ የታለመ ሽፋን መሆኑም መጠርጠር የዋሃነት አያሰኝም።
በክልሉ የሃይማኖት ግጭትና ጦርነት በማስነሳት ወደ ተለያዩ ሀገሪቷ ክፍሎች እንዲዘመት በማድረግ የፖለቲካና የስልጣን ፍላጎት በሽብራዊ ስልት፣ ሃይማኖትን እንደጋሻ፣ መሸሸጊያና መደበቂያ በመጠቀም እውን ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች አባል፣ አማካሪ፣ ቃለ አቀባይና ተዋናይ መሆኑ ተግባሮች ከምስክር በላይ ጮሆው ይናገራል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ”እውነተኛ ሃይማኖት አባት ጠፋ” የተበለውም እንደዚህ አይነት ሰዎች ከእምነት ይልቅ የፖለቲካ ወገንተኛነት ያደሉ ሰዎች እንደ አሸን መፍላት አገራችን ወዴት እያመራቸነው የሚለው ጥያቄ አስፈሪ ያድርገዋል።
የእምነት አባቶች ሰላም የሚፈጠር፣ እውነተኛ፣ ሃቀኛ፣ ታማኝ፣ አስታራቂ፣ መካሪ፣ ይቅርባይ፣ አስተማሪ፣ አዛኝ፣ ሩህሩህና ሆደ ሰፊ ሆኖ ለአገርና ህዝብ የሚጠቅም መልካም አሻራ የሚያሳርፉ እንጂ በውሸት ፈጠራ አገርና ህዝብ የሚያተራማስ እንዳልሆነ በአገራችን ታሪክ አልተመዘገበም።
ከሃይማኖት አላማ ይልቅ በአቋራጭ ስልጣን ፈላጊዎች አላማና ድጋፍ ለመሆን የእምነት ተቋማት ኃላፊነት በመጠቀም የፖለቲካ አስፈፃሚዎች ሆነው ሀገር በማመስ የተከኑ ሰዎች አገሪቷን ሰላማን እያሳጧት መምጣት አሳሳቢና አስጨናቂ አድርጎታል።
ወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ሁለት ካባ ደራቢ ተኩሏዎች ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የራስን የብሔርና የእምነት የበላይነት ለመጎናፀፍ እንደመሳሪያ እየተጠቀሙ፣ እምነትን ከእምነት፣ ብሔርን ከብሔር፣ ህዝብና መንግስትን በማጋጨት ትርፍ መሰብስብ የሚፈልጎ ዳቢሎሳዊያን ስብስብ መብዛታቸው አሳኝ ወቅት አድርጎታል።
የሐረሪ ክልሉ የሰላም፣ የመቻቻል፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የአብሮነት መቅደስና እና አድባር ነው። የሐረር ከተማ በ200 ሜትር ሬዲየስ ውስጥ የተለያዩ እምነቶች፣ የኦሮቶዶክስ፣ የካቶሊክና የእስልምና ቤተ እምነቶች አብሮ መኖር ከጀመሩ ከመቶ ሃያ አመት በላይ
ዘመናት ግጭት ሳይከሰት በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት በመዝለቃቸው ለአለም ድንቅ እሴት ያበረከቱ ተቋሞች ናቸው።
ይህን ድንቅ መልካም አሴትን ለማደፍረስ የፖለቲካ ቁማር ትርፍ ለመቸብቸብ ሲሉ የህዝቦችን አንድነትና ሰላም የማናጋት ሴራ በእምነት ተቋማን ተገን መፈፀሙ ወራዳና ሴይጣናዊ ተግባር ነው።
በማንኛውም እምነትና ተቋምና ምእመናን የሚፈፀም ጥቃት በማንኛውም ሰብአዊ ሚዘናዊ አስተሳሰብ የሚደገፍ ተግባር አይደለም። በእምነት ተቋማት፣ በምእመናንና በማንኛውም ዜጋ ጥቃትና ጉዳት ማድረስ፣ ሃይማኖታዊ በአላት ስርዓት ማወክና ማደናቀፍ፣ በዜጎች ሀብትና ንብረት ላይ የሚፈፀም ትንኮሳና ጥቃት የሚኮነን፣ የሚነቀፍና የማይደገፍ በማንኛውም እምነት፣ ሞራልና ግብረገብነት የሚወገዝ ተግባር ነው።
የጥመቀት በአል አከባበርን ጋር በተያየዘ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ፓትሪያርክ ብፅወ ወቁዱስ አቡና መርቆሪዩስ በጉንደር፣ በሐረርና ድሬደዋ ከተማ የተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ በጋዜጠኞች ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ነበር። በጉንደር ከተማ ከበአሉ አከባበር ጋር ለበአሉ የተዘጋጀው መድረክ ርብረብ በመደርመሱ የተከሰተው ምዕመናን ሞትና የአካል ጉዳት አደጋውን ገልፀው፣ በአደጋው መድረስ ማዘናቸው እና ጉዳት የደረሰባቸውን በማፅናናት ብፅእ መልክት አስተላልፈዋል።
በመቀጠልም ፓትሪያርኩ በድሬደዋና በሐረር ከተማ የተከሰተውን ችግር በሶሽል ሚዲያና ሚዲያ የሚወራው ነገር ብንሰማም፣ ይህን በመንተራስ፣ የችግሩ ምንጭ በአግባቡ ሳይጣራ የምሰጠው መግለጫ የለም በማለት በተደጋጋሚ በጋዜጠኞች የተነሳባቸውን ጥያቄ፣ በበሰለ፣ አስተዋይነትና ኃላፊነት የተሞለበት ምላሽ መስጠታቸው የሚደነቅ ተግባር አሳይተዋል።
እነ ብፅወ አቡነ ማቃሪዩስ መግለጫ ግን ከእምነቱና ከተቋሙ ተፃራሪ የቆመ፣ የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ፣ በእምነቶች፣ በብሔሮች፣ በህዝቦች መካከል አለመተማመንና ግጭት የሚፈጥር፣ የክልሉን ሰላምና መቻቻል እሴት የሚያደፈርስ እኩይ ተግባር መሯሯጥ የሚያሳዝን፣ የማያሳፍር፣ የሚያስደነግጥና ከአንድ እምነት አባት የማይጠበቅ ምግባር ነው።
ስለዚህም የዚህ አይነት ሰውና አዝማሚያ ለአገር ፅርና ጥፋት ስለሆነ ከበስተጀርባ ያለው ፍላጎት፣ ሴራና ተንኮል፣ ፖለቲካ፣ ስልጣን፣ እምነት በጥንቃቄ ተይቶ እኩይ ተግባሩ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት።
አፌው ወጠኒ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*