የትላንቱን እውነተኛ ታሪክ በቅጡ ያላወቁ
በውሸት ታሪክ በባለታሪኩ ድንገት ተመፃደቁ
~•~
የሀረሪ ሕዝብ ለእልፍ አመታት የነፃነት ታሪክ ያለውና የራሱ ባህልና ቋንቋ የማንነት መገለጫዎች መካከልም ህያው ቅርሶቻቸው ናቸው፡፡
በምስራቅ አፍሪካ ሀረርን ለሞዴልነት ያበቃው የሀረሪዎች ነፃ የመንግስት አስተዳደር፤ የሀረሪ ሕዝብ የረዥም ዘመናት ታሪክ ባህልና ቋንቋው እንዲሁም በነፃ መንግስት አስተዳደሩ መናገሻና የዳበረው ባህላዊ እውቀቱና ጥበብ ያንፀባረቀበት ጀጎል ከማንነት መገለጫዎቹ መካከል ህያው ቅርሶቻቸው ናቸው፡፡
የሀረሪ ሕዝብ ከመጀመሪያው አሚር ሐቦብ ከ969-1000 እ.ኤ.አ እስከ መጨረሻው መሪ አሚር #አብዱላሂ እ.ኤ.አ ከ1885-1887 ሰባ ሁለት አሚሮች በተፈራረቁበት ሉአላዊ መንግስት ራሱን ሲያስተዳድር ቆይቷል፡፡ የምስራቁን ክፍል በተለያዩ የጎሳና ባህላዊ አስተዳደሮች በተዋቀረ በሱልጣናት ሲተዳደር ከቆየ በኋላ በዘመናዊ አሚር አስተዳደር መመራት የጀመረው የሐረር ከተማን በ8ተኛው ክፍለ ዘመን በመቆርቆር የሥርዓቱ መናገሻ ማዕከል ካደረገ ወዲህ ነበር፡፡
የሐረሪ ነገስታት ከአለም አቀፍ ህግ አንፃር
የሐረሪዎች አሚሮች/ሱልጣኖች/ኢማም/ መንግስታት እንደ ነፃ መንግስት ነበሩ ወይ የሚለውን በአለም አቀፍ ህግ መመዘኛ አንፃር ለማየት እንሞክራለን።
በተራ አገላለፅ በአለም አቀፍ ህግና ስምምነት አንድ ህጋዊነት ያለው ሀገር በአንድ ማዕከላዊ መንግስት የሚመራና በግዛቱ ሉአለዊነት ስልጣን ባለቤትነት ያለው ነው።
በአለም አቀፍ ህግ ሉአላዊ ሀገር የሚባለው
- ቋሚ ህዝብ ያለው(permanent population)
2.የተረጋገጠ ግዛት ያለው(defined teritory) 3.ቋሚ መንግስት ያለው( one/permanent gevernment)
4.ከሌላ ነፃ ከሆነ ሀገር ጋር የግንኙት ስምምነት የመፍጠር አቅም ያለው (the capacity to enter into relations with other sovereign states or treaty making power)
ከእነዚህ አለም አቀፍ መመዛኛ ነጥቦች የሐረሪ ህዝብ መንግስት እንዴት ይቃኛል የሚለውን በደምሳሳና በአጭሩ ለማየት እንሞክራለን።
- ቋሚ ህዝብ ያለው(permanent population)
አንደ ህዝብ እንደ ቋሚ መመዘኛ ከሚወሰድባቸው ነጥቦች፦ የሀረሪ ሕዝብ ለእልፍ አመታት የነፃነት ታሪክ ያለውና የራሱ ባህልና ቋንቋ የማንነት መገለጫዎች መካከልም ህያው ቅርሶቻቸው ናቸው፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ሀረርን ለሞዴልነት ያበቃው የሀረሪዎች ነፃ የመንግስት አስተዳደር፤ የሀረሪ ሕዝብ የረዥም ዘመናት ታሪክ ባህልና ቋንቋው እንዲሁም በነፃ መንግስት አስተዳደሩ መናገሻና እምብርት የዳበረው ባህላዊ እውቀቱና ጥበብ የንፀባረቀበት ጀጎል ከማንነት መገለጫዎቹ መካከል ህያው ቅርሶቻቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ታሪካዊ አሻራዊች የሚያንፀባርቅው አንደኛው የአለም አቀፍ መመዘኛ አንድ ህዝብ በህዝብነት በቋማነት የመኖርን የሚያመለክት ነው።
2.የተረጋገጠ ግዛት ያለው(defined teritory)
የሐረሪ አሚሮች የምስራቅና ደቡብን ክፍል በተረጋጋ ሁኔታ 969 ዓ/ም እስከ 1887 ዓ/ም ድረስ የራሳቸውን ግዛት በነፃ ሲያስተዳድሩ ነበር። አከባቢው የምስራቁን ክፍል በተለያዩ የጎሳና ባህላዊ አስተዳደሮች በተዋቀረ በሱልጣናት ሲተዳደር ከቆየ በኋላ በዘመናዊ አሚር አስተዳደር መመስረታት የጀመረው የሐረር ከተማን በ8ተኛው ክፍለ ዘመን በመቆርቆር የሥርዓቱ መናገሻ ማዕከል ካደረገ ወዲህ መህኑ ይታወቃል፡፡ ሐረር የዋና ከተማና ወታደራዊ ማዕከል ከሆነች ወዲህ በአፍሪካ ቀንድ ታሪክ የሐረርና ሐረሪዎች ሚና ጎልቶ የሚታይ እንዲሆን አስችሏል። በዚህ ዘመን አብዛኛው አፍሪካ ሀገራት ራሳቸውን የቻለ መንግስታትና ግዛት አልነበራቸውም።
የሐረሪ ህዝብ ከ1ሺህ ዓመት በላይ በተለያዩ ግዜያት እየሰፈና እየጠበበ ከዘይላ እስከ ሸዋ መካከል ያለውን ምድር የሚያጠቃልል ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩ እንደነበር ይታወቃል።
ሐረሪዎች ከዚህም በተጨማሪ ሐበሽን ለማቅናትና አንድ ለማድረግ ኢትዮጵያት ከሰፊ ግዛት ጋር ለማቌቌም ከማንኛውም አፄዎች በተሻለ ሁኔታ ለመመስረት የሞከረው ኢማም አህመድ አልጋዚ ነበር። የአሁና ኢትዮጵያ፣ ኤርትራን፣ የሱዳን ኑቢያ ግዛት፣ ብሪትሽ ሶማሌ ላንድን፣ ኢታሊ ሶማሌ ላንድን እና ፍሬንች ሶማሌ ላንድ(የአሁና ጁቡቲ) በማጠቃለል በአንድ ሀገር ጥላ ስር ለአስራ አምስት አመታት 1527-1554 ዓ/ም አስተዳድራል።
ሐረሪዎች የተረጋጋና የተረጋገጠ ግዛት ለምእተ አመታት እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል። ከዚህ አንፃርም ሁለተኛው የተረጋገጠ ግዛት አለም አቀፍ መመዘኛ (defined teritory) የነበራቸው መሆኑ ሉአላዊ ህዝብ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
- ቋሚ መንግስት ያለው( permanent/one gevernment)
የሀረሪ ሕዝብ ከመጀመሪያው አሚር ሐቦብ ከ969-1000 እ.ኤ.አ እስከ መጨረሻው መሪ አሚር አብዱላሂ እ.ኤ.አ ከ1885-1887 ሰባ ሁለት አሚሮች በተፈራረቁበት ሉአላዊ መንግስት ራሱን ሲያስተዳድር ቆይቷል። በዚያን አስተዳደር ዘመን በtraditional ፌድራል ሲስተም ሁሉም አካባቢያቸው ራሰቸው በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በመፍቀድ በማአከላዊነት መንግስት በኢማሙ ስር ይገዙ ነበር። ይህ ደግሞ ሶስተኛው በአለም አቀፍ መመዘኛ ቋሚ መንግስት ( permanent/one gevernment) ለዘመናት የነበራቸው መሆኑን ያመለክታል።
- ከሌላ ነፃ ከሆነ ሀገር ጋር የግንኙት ስምምነት የመፍጠር አቅም ያለው (the capacity to enter into relations with other sovereign states or treaty making power)
የሐረር አሚሮች የራሳቸውን ገንዘብ በማተም ሐረር የራስዋ መገበያያ ገንዘብ ያላት እንድትሆን በማድረግና ሰፊ አካባቢን ያካለለ የንግድ እንቅስቃሴ በመዘርጋት በርበራ፣ ዘይላና ታጁራም የውጭ ንግድ በሮችዋ የነበሩ ሲሆን የውጪ ንግድ በቀይ ባህር እስከ ምፅዋ፣ በህንድ ውቅያኖስ ከፋርስ ባሻገር ደግሞ እስከ ቦምቤይ ተስፋፍቶ ነበር፡፡
የሐረሪ ገዢዎች የአለም አቀፍ ግንኙነት አንፃር ከቻይና፣ ከቱርክ፣ ከህንድ፣ ከግብፅ፣ ከየመን፣ ከሞሮኮ፣ ከሩቅ ምስራቅና ከአረቡ አለም ጋር የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ የሃይማኖት፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እና የጦር እገዛና ስምምነት ግንኙነት እንደነበራቸው ታሪክ ያስረዳል። በአንድ ዘመን ለቱርክ መንግስት እርዳታ የሰጡበት ጊዜም ነበር። በዚህ ረገድም አራተኛው አለም አቀፍ መመዘኛ ከሌሎች ነፃ ከሆነ ሀገራት ጋር የግንኙት ስምምነት የመፍጠር አቅም የነበራቸው ነፃ መንግስት እንደነበሩ ነው።
በአጠቃላይ ሐረሪ ህዝብ የእስልምና ኃይማኖት ትምህርት፣ የአለም አቀፍ ንግድ አንቅስቃሴና ባሕላዊ ስነ-ጥበባት ማዕከል፣ የከተማ ኑሮ ዘዴና ባህል በተለይም ዘመናዊ መንግስት ሥርዓት /state craft/ እንዲመሰረትና እንዲስፋፉ ከማድረጉም በላይ የአለም ቅርስ ተብሎ የተሰየመውን የሐረር ጀጎል ለአለም ሕዝብ ለማበርከት ያበቃ የራሳቸው ማንነት መገለጫ የሆኑ የዳበረ ባህላዊና ልማዳዊ እውቀት ባለቤት ናቸው፡፡ ስለሆነም ሐረሪዎችና ሐረር በመንግስት አስተዳደር ሥርዓትና ወታደራዊ ጥበብ፣ በሥነ-ሕንጻ ጥበብ፣ በባህላዊ ጌጣጌጥና ሥነጥበባት፣ በግብርና አስተራረስ ዘዴ እንዲሁም በባህላዊ ኪነጥበባትና ኀይማኖታዊ ትምህርት እንዲሁም በባህላዊ ህክምና ጥበብ የተካኑ የአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢው ፈርጥ እና ተምሳሌት ለመሆን በቅተው እንደነበር ታሪክ ያወሳል።
የሩቅ ጠላቶች እንዲሁም በሰሜኑ ክርስትያንና በምስራቁ ሙስሊም መካከል ለብዙ ምዕተ ዓመታት አንዱ ሌላውን ተፅእኖው ስር ለማሳደር ወይም ለማስገበር የተካሄዱ በርካታ ግጭቶችና በመካከላቸው ከፍተኛ ፍጥጫ ለዘመናት ከዘለቀ በኋላ የአቢሲኒያ ሰለሞናዊን ነገስታት የሐረርጌ አካባቢዎችንና የነዚህ አካባቢዎች ማዕከል የሆነችውን ሐረርን የመቆጣጠር የረዥም ጊዜ ህልም ከፍተኛ እልቂት ባስከተለውና ‹‹ለማስገበር›› በአፄ ምኒልክ ሠራዊት በተካሄደው የጨለንቆው ጦርነት በኃላ የሐረሪ ህዝብ ሉአላዊነት እንዲያጣ ሆኗል፡፡
የሐረሪ ህዝብ ከ1ሺህ ዓመት በላይ በተለያዩ ግዜያት እየሰፈና እየጠበበ ከዘይላ እስከ ሸዋ መካከል ያለውን ምድር የሚያጠቃልል ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩ 72 አሚሮች የተፈራረቁበት ሉአላዊ መንግስታት የነበሩት ህዝብ ነው፡፡ ታዋቂው እንግሊዛዊ ታሪክ ጸሀፊና ዲፕሎማት ሪቻርድ በርተን እ.አ.አ.1855 ሐረር የራሳ ሉአላዊ መንግስት በነበራት ወቅት ጎብኝቶ በጻፈው ”The First Foot step in Eastern Africa’’ በሚል መጽሐፍ ‹‹ታሪካዊ የሆነች የአንድ ኀያል ብሔረሰብ ከተማ፤ የምሥራቅ አፍሪካ መነሐሪያ፤ የትምህርትና የስነ ጥበብ ማእከል፤ በግንብ የታጠረችና በድንጋይ የተሰሩ ቤቶች ያላት፤ በተወላጅ መሪዎቿ የምትገዛ ነፃ ሀገር፤ ከአካባቢ ጎሳዎች የተለየ የግል ቋንቋ እንዲሁም የመገበያያ ገንዘብ ያላት፤ የቡና ንግድ መዕከል፤ የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች አምራች፤ የባርያ ንግድ መዕከል›› ብሎ ሐረርን ገልጻት ነበር፡፡
የሐረሪ ነገስታት በአለም አቀፍ ህግ ሉአላዊ ሀገር እንደነበሩ፦ ቋሚና የተረጋጋ ህዝብ እንደነበራቸው፣ የተረጋገጠ ግዛት እንደነበራቸው፣ ቋሚ መንግስታት በተከታታይ የነበራቸው እና ከሌሎች ነፃ ሀገራት ጋር ነፃ የግንኙት ስምምነት የመፍጠር አቅም ኖራቸው የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ የሃይማኖት፣ ወታደራዊ፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል።
ሐረር የዋና ከተማና ወታደራዊ ማዕከል ከሆነች ወዲህ በአፍሪካ ቀንድ ታሪክ የሐረርና ሐረሪዎች ሚና ጎልቶ የሚታይ እንዲሆን አስችሏል።
የሐረር አሚሮች የራሳቸውን ገንዘብ በማተም ሐረር የራስዋ መገበያያ ገንዘብ ያላት እንድትሆን በማድረግና ሰፊ አካባቢን ያካለለ የንግድ እንቅስቃሴ በመዘርጋት በርበራ፣ ዘይላና ታጁራም የውጭ ንግድ በሮችዋ የነበሩ ሲሆን የውጪ ንግድ በቀይ ባህር እስከ ምፅዋ፣ በህንድ ውቅያኖስ ከፋርስ ባሻገር ደግሞ እስከ ቦምቤይ ተስፋፍቶ ነበር፡፡
በአጠቃላይ ሐረሪ ህዝብ የእስልምና ኃይማኖት ትምህርት፣ የአለም አቀፍ ንግድ አንቅስቃሴና ባሕላዊ ስነ-ጥበባት ማዕከል፣ የከተማ ኑሮ ዘዴና ባህል በተለይም ዘመናዊ መንግስት ሥርዓት /state craft/ እንዲመሰረትና እንዲስፋፉ ከማድረጉም በላይ የአለም ቅርጽ ተብሎ የተሰየመውን የሐረር ጀጎል ለአለም ሕዝብ ለማበርከት ያበቃ የራሳቸው ማንነት መገለጫ የሆኑ የዳበረ ባህላዊና ልማዳዊ እውቀት ባለቤት ናቸው፡፡
ስለሆነም ሐረሪዎችና ሐረር በመንግስት አስተዳደር ሥርዓትና ወታደራዊ ጥበብ፣ በሥነ-ሕንጻ ጥበብ፣ በባህላዊ ጌጣጌጥና ሥነጥበባት ፣በግብርና አስተራረስ ዘዴ እንዲሁም በባህላዊ ኪነጥበባትና ኀይማኖታዊ ትምህርት እንዲሁም በባህላዊ ህክምና ጥበብ የተካኑ የአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢው ፈርጥ እና ተምሳሌት ለመሆን በቅተው እንደነበር ታሪክ ያወሳል።
የሩቅ ጠላቶች እንዲሁም በሰሜኑ ክርስትያንና በምስራቁ ሙስሊም መካከል ለብዙ ምዕተ ዓመታት አንዱ ሌላውን ተጽዕኖው ስር ለማሳደር ወይም ለማስገበር የተካሄዱ በርካታ ግጭቶችና በመካከላቸው ከፍተኛ ፍጥጫ ለዘመናት ከዘለቀ በኋላ የአቢሲኒያ ሰለሞናዊን ነገስታት የሀረርጌ አካባቢዎችንና የነዚህ አካባቢዎች ማዕከል የሆነችውን ሀረርን የመቆጣጠር የረዥም ጊዜ ህልም ከፍተኛ እልቂት ባስከተለውና ‹‹ለማስገበር›› በአፄ ምኒልክ ሠራዊት በተካሄደው የጨለንቆው ጦርነት ተደመደመ፡፡
ስለሆነም የሀረሪ ህዝብ ነፃ መንግስት ፈርሶ በአፄው ማዕከላዊ አስተዳደር ሥር በመጠቃለሉ የሀረሪ ሕዝብም ነፃ አስዳደሩን ተቀማ፡፡
በአጠቃላይ ሰብዓዊ መብቱና ክብሩ እንዲሁም የራስን በራስ ማስተዳር መብቱን ጨምሮ የረዥም ዘመናት ታሪኩና የማንነት መገለጫ ባህላዊ ቅርሶቹ አደጋ ላይ ወደቁ፡፡
ባለፈው ስርዓት የሀረሪ ህዝብ ሉላዓዊነቱ ተነጥቆ በርካታ ሰብዓዊ ግፍ በማንነቱ ሲፈፀምበት ቆይታል። ሀረሪዎች ግዛታቸው ተነጥቀው በኢኮኖሚያዊ ማኃበራዊ እና በፖለቲካ ተሳትፎ ባይተዋር እንዲሆኑ በማድረግ ከቄያቸው እንዲፈነቀሉና እንዲሰደዱ ተደርገው አናሳ(minority) እንዲሆኑ ተደርገዋል።
በመሆኑም ሐረሪዎች ሉአላዊነታቸው ተነፍጎ ከ100 ዓመት በላይ ባለፈው አድሎአዊ ሥርዓት ለተለያዩ ብዝበዛና ጭቆና ተጋልጠዋል፡፡
ከሰብዓዊ ህይወት ጀምሮ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርገዋል። እነዚህን ጨቋኝ የዘውድ አገዛዝና የአምባገነኑን ወታደራዊ ሥርዓት በደል የሐረሪ ህዝብ እጁን አጣጥፎ በመቀመጥ ያስተናገደበት አንድም ግዜ አልነበረም። ይልቁንስ በተለያዩ ግዜዎች በገዢዎች አጸፋዊ ምላሽ ሳይምበረከክ አምሮ ታግሏል። ለሺ ዓመታት ያቆየውን ቋንቋውን፣ ባሕሉንና ቅርጹን ለትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲከበር እንደሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል።
ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠየቀቸው ምክንያት የከፋ ግልጽና ስውር የብዝበዛና ጭቆና ተጭኖባቸው ሐረሪዎች በታሪካዊ መኖሪያቸው አናሳ ሊሆኑ ችለዋል።
ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ኢትዮጲያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ጨቋኞቹ ዘውዳዊ ሥርዓትን ተክተሎም የነበረው አምባገነናዊው የወታደራዊ መንግስት ብዙሕነትን(diversity)ና የህዝቦች ማንነትን በመካድ የገነቡት ፀረ -ዲሞክራሲያዊና አሐዳዊ አገዛዝ ለዘመናት ሀገራችንን ሰላምና መረጋጋትን በማሳጣት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃ ሕዝቦቿም ለድርቅ፣ ለረሀብና ለኋላ ቀርነት ተዳርገው እዲሰቃዩ ምክንያት ሆኖ ነበር። ከረጅምና እልህ አስጨራሽ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ የነፍጠኛውን የብዝበዛና የጭቆና ስርዓት ያስቀጠለው ወታደራዊው የደርግ መንግስት ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ኃይሎች አስተባበሪነትና ፈፃሚነት በህዝቡ መራራ ትግል ሊወገድ ቻለ።
ከደርግ ውድቀት ብኃላ ካለፉት ሥርአቶች በተለየ ሁኔታ የህዝቦች ነፃነት፣ የብሄሮችና የሀይማኖቶች እኩልነት እንዲሁም ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የተረጋገጠባት አዲሲቷን ኢትዮጲያ ለመመስረት ቃል በገቡት መሰረት ሰኔ 24/1983 ዓ.ም. ብሔራዊ ኮንፈረንስ በማካሄድ የሽግግር መንግስቱ ተመሰረተ።
የኮንፈረንሱ ትልቅ ውጤት የሽግግር መንግስቱ መመስረትና የሚተዳደርበት ቻርተር መጽደቁ ነበር። ቻርተሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ የእኩልነት መብቶች እንዲሁም ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ራስን በራስ የማስተዳደር መብት፣ ማንነታቸውን፣ ባህላቸውንና ታሪካቸውን የመግለጽ፣ በቋንቋው የመጠቀምና የማሳደግ መብት ተረጋገጠ።
የብሔሮች ራስን በራስ የማስተዳደር ዝርዝር አፈጻጸሙን በተመለከተም የሽግግሩ መንግስት ምክር ቤት ባወጣቸው አዋጆች በይፋ ተገለጸ። በተግባርም 14 ክልሎችና በርካታ ወረዳዎች ተቋቅመው ብሄሮች ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር በቁ። በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የብሔሮች መብትና እኩልነት ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባ ገና ከጅምሩ ሲጠነሰስ የነበረው አስተሳሰብ እውን ሆነ።
የሀረሪ ሕዝብን ጨምሮ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት ያነሱዋቸው ጥያቄዎች ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ ምላሽ የሚሰጥ ሥርዓት መፈጠሩን ያመላካተው የሽግግር መንግስቱ ቻርተር እዲሁም በመሉ ፈቃዳቸው በፀደቀ የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት ለዘለቄታው ምላሽ አግኝቷል፡፡
የሀረሪን ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ መብት መረጋገጥ ያበሰረው የክልል አስተዳደር መወሰን፤ የሽግግር ወቅት ቻርተሩ ባረጋገጠው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለማስፈጸም የሽግግሩ መንግስት ምክር ቤት በ1984 ዓ.ም. ብሄራዊና ክልላዊ የራስ አስተዳደር መንግስታትን ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ክልል 13 የሐረሪ ክልል እንዲሆን በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ (weighted majority) ወሰነ። ይህም ሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በየደረጃው ራሳቸውን ለማስተዳደር ያስቻለ ነው። የአብዮታዊ ዲምክራሲ ኃይሉ ለረጅም አመታት የአናሳውም የብዙሐኑም ብሄር መብት ለማረጋገጥ ያደረገው መራራ ትግል ተግባራዊ ውጤት መገለጫ ነበር ማለት ይቻላል። በሌላ በኩል የሐረሪ ህዝብ ለመቶ አመታት የተነፈገው ሉአላዊነት ዳግም የተረጋገጠበት ውሳኔ ነበር።
በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስትም ይኸው ውሳኔ በአንቀጽ 47 (9) በዘላቂና ቋሚ መሠረት ላይ እንዲተከል ሆነ፡፡ በዚህም መሰረት በፌደራል ህገመንግስቱ ከዘጠኙ የፌደሬሽኑ አባል ክልሎች መካከል የሐረሪ ክልል አንዷ ሆነች።
የፌድራል ሥርዓት የማይቀበሉ የድሮ ስርአት ናፋቂ አመለካከት አራማጆች ይህንኑ ሂደት ሲተቹ ይስተዋላሉ፡፡ ይኸው ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ-መንግስታዊ መብት የብሄሮችን የቁጥር መጠን ወይም የግዛት ስፋት መጠንን መሠረት ያደረገ አይደለም፡፡ የብሄሩ አሠፋፈር መልካአምድራዊ አቀማመጥና ሥነልቦናዊ ትስስር መሰረታዊ ነጥቦች መካከል የሚወሰዱ ናቸው፡፡
እስቲ እግረመንገዴን በጭፍን ጥላቻ የተለወሰ ምቀኝነት ተደናብረው ለሚቦርቁ ጭፍኖች በጥቂቱ ማስገንዘቢያ ነጥቦችን ላመላክታቸው።
- የሀረሪ መብትን ለማወቅና ለማክበር የሀረሪን ህዝብ ታሪክ በሚገባ መመርመር ያስፈልጋል።
- የክልሉን አመሰራረት በሚገባ ማወቅ፣
- የነባር( indeginous)ህዝቦች መብት የአለም አቀፍ ህጎችን ማወቅ፣
- የፌድራል ስርዓት አመሰራረትና
አወቃቀር( በተለይም ደግሞ mulitiethinic
ferderal system የሚከተሉ ሀገረት ቤልጅየም፣
ናይጄሪያ ሌሎች ህንድ፣ ሩሲያ…… የመሳሰሉትን
መቃኘት፣ - የአውንታዊ (affermative action) መብት፣
- የአናሳውች(minority right) አከባበር እና የራስ አስተዳደር መብት ያጎናፀፉ ሀገራት ለምሳል የአለም አቀፍ ልምዶች፦
- ክሮሽያ ውስጥ 8 ለሚሆኑ አናሳ ብሔርች መብት፣
- ሴንጋፖር ላይ ማላይ፣ ህንዶች እና ሌሎች አናሳዎች መብት፣
- እስሎቫክ ላይ ለሐንጋሪውችና ጣሊያኖች፣
- ጆርዳን ላይ ለክርስትያኖችና ለኮሮሽያኖች፣
- ፓኪስታን ላይ ሙስሊም ላልሆኑ አናሳውች፣
- ኮሎምቢያ ላይ ለጥቁሮችና ለነባር ህዝቦች፣
- ኒውዝላንድ ላይ ለማኦሪ ህዝቦች፣
- ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ስዊድን ላይ ለነባር ሳሚ አናሳ ህዝቦች፣
- ፖላንድ ላይ ለጀርመን አናሳውች፣
- ህንድ ላይ ለሼዙልድ አናሳ ጎሳውች፣
- ፊጂ(Fiji) ላይ ነባር ፊጂውች፣ ለህንድ ፊጅውች፣ ለሮቱማንሶች እና ሌሎች አናሳውች፤
የራስ አስተዳደር፣ ልዩ የምክር ቤት ወንበር ውክልና በመዕከላዊ መንግስት እና በራሳቸው ግዛት መብት ተሰጥቶቸዋል።
የሀረሪ ህዝብም በማንነቱ ራሱን በራሱ የመወሰንና የማስተዳደር መብት ተፈጥሮዋዊና ህገ መንግስታዊ መብት የተጎናፀፈው መብት ነው። እንጂ ማንም ደስ ስላለው አንስቶ የተሰጠው መብት አለመሆኑን መገንዘብ ግድ ይላል። የማንነት መብት በህዝብ ቁጥር አናሳነትና በፐርሰንት ስሌት አይደፈቅም።
በውሸት ያለማስረጃ ለምትዘባርቁት ግለሰቦች እና ቡድኖች በእውነት ማስረጃ የተደገፈ ተነግሮ የማያልቅ በአለም ህዝብ የሚታወቅ ታሪካችንን በማንኪያ ሳይሆን በጭልፍ ማጉረሳችን ይቀጥላል ለዛሬው እዚህ ላይ አበቃለሁ ።
ቸር እንሰንብት