19 ሰው ሰራሽ ኦርጋኒክ ኦርጋኒክ ያልሆኑ ኮሮናዎች

19 ሰው ሰራሽ ኦርጋኒክ ኦርጋኒክ ያልሆኑ ኮሮናዎች

ፍትሃዊነት ፣እኩልነትት እና ሰብአዊነት አዳካሚዎች
በ ፕሮፌሰር አብዲ ኸሊል
ፅሁፍ በ ኢማን ጃሚእ


ሰው ሰራሽ ኮሮናዎች የሁሉንም ሰው ሰብአዊነት አካል ላይ ጥቃት አድርሰዋል ።
አሁን ያለንበት ወቅት ከ ኮቪድ–19 አውሎ ንፋስ ጋር አስደንጋጭ ነው።በሰው ልጅ ታሪክ ኮቪድ-19 አለምን ውደ ሌላ አቅጣጫ ቀይሯል። በሽታው በርካታ የሰው ልጅ አስተዳደር ድባብ ስርአቶችን በራሱ መልክ መቀየር ችሏል።
ለምሳሌ ፦ ካፒታሊዝም ፣ ኮሚኒዝም እና ብዙ ተጨማሪ- isms ችን እና በተጨማሪም ከባድ የሰው ልጅ ስቃይ ብሎም ለተፈጥሮ ውበት ጥፍት ሁነኛ ተጠቃሽ ምክንያት ነው።እንዲሁም በመንፈሳዊ አተገባበር ዙሪያ ለተከሰቱ የአምልኮ ስርአት መዛባት እና ለመሳሰሉትም ።
እኔ የጤና ባለሞያዎች የሚሰጡትን ምክር በመቀበል እና በመስማት እቤት እቆያለሁ ግን ይህ በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ የማያታወቅ አሳዛኝ ክስተትና ሁኔታ በአለም አቀፍ ደረጃ በሰው ልጆች ባህሪያት እና አስተዳደራዊ መዋቅሮች ላይ ያደረሰውን መጠነ ሰፊ ቀውስ እንድመለከተው አደረገኝ ።
ኢሰብአዊነት አስተሳሰብን እንደገና መመርመር !
ብጥብጥ ለምን አስፈለገ ?
ወደዚህ ያመጣን ምንድነው?
በአለማችን ዙሪያ ያሉ ህመሞችስ ምንድናቸው?
ፋቃደኝነታችንን አለአግባብ ተጠቅመንበታል?
የፍረኦን ዘርስ ሆነናል?
ስለ ማህበራዊ ጉዳዮቻችን የምናስብበት ጊዜ አይደለም? አለም እኩልነት፣ ፍትህ እና ሰላም በናፈቀችበት በዚህ ጊዜ እራሳችንን ለውጠን ወደ ሰብአዊነት የምንመለስበት ጊዜ አይደለምን?
ኮቪድ-19 በሰው ልጅ ጤና ፣ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ ኑሮ ፣ በፖለቲካው ባጣቃለይ ይህ ነው የማይባል ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
በተናጥል አንድን ሰው ማጣት ለቤተሰብ እና ለህብረተሰብ ትልቅ የአደጋ አሳዛኝ ክስተትም ነው። አንድ የሚወዱትን ሰው ላጡ ሰዎች ከፍተኛ አዘኔታና የልብ ስብራት እና ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል።ለቤተሰብ የሚታዩና የማይታዩ የተለያዩ አሉታዊ መዘዞች ትልቅ ናቸው።ግን ይህ አሳማሚና አሳዛኝ ክስተት ያለፈው የኛ የአስረተ አመታት ማህበራዊ መነሻችን እንድናገናዝብ ያደርገናል። ለዚህ የዳረጉን ኢሰብአዊ ስርአቶችና ተግባሮቻችን መልሰን እንድንገመግማቸው የሚያደርገን የማንቂያ ደውል ነው።በግል ፣በቡድን ፣ በሃገር አቀፍ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ሃላፊነትን የምንወስድበት ጊዜው አሁን ነው ።እራሳችንን በማስተካከል ፣የተጓዝንበትን አቅጣጫ በማረም ወደ ትክክለኛው ሰብአዊነት መመለስ ነው።
የተለያዩ አሉታዊ ፣ አውንታዊ ፣ተቃራኒ፣ እና ደጋፊ የሆኑ ከዚህ ወረርሺኝ የተማርነው ትምርቶች አሉ።በቅድመ ኮቪድ-19 ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዓለም ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ ደርሰዋል ፡፡ ለአብነት ያህል ኢሰብአዊነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ የስነምግባር ብልሹነት፣አክራሪነት ፣ረሀብ፣ ድህነት፣ ጦርነቶች ፣የኃይል አጠቃቀም ብሎም በካፒታሊዝም እና በኮሚኒዝም ርዕዮተ አለም የበላይነት ጭቆና ምክንያት የተፈጥሮ ብዝበበዛ እና የተፈጠሮ ሃብትን ያለ አግባብ የመጠቀም ሁኔታ በመላው አለም ማእዘናት ይስተዋሉ ነበር ።እነዚህ ርዕዮተ አለሞች ቤተሰቦች ፣የህብረተሰብ ክፋሎች ፣ማህበረሰቦችና ሐገሮች ላይ እጅግ መጠነ ሰፊ ጉዳት በማድረስ አጥፍተዋቸዋል።የተፈጥሮንና የሰው ዘር ሰብአዊነት ሚዛን በማናጋት አፍርሰው አጥፍተዋል።እነዚህ ርዕዮተ ዓለም አዲሱን ትውልድ በራስ የመተማመን መንፈስ በአጋጣሚ እንደሚኖር የአዕናፈ ሰማይ የጭለማ ስእል በማሳየት የሰው ልጅ ከሰብአዊነት በላይ በቁሳዊ ንዋይ እንዲመዘን ማድረግ ችለዋል። እነዚህ በዋናነት በቫይረሱ የተያዙ ናቸው የግሎባላይዜሽን ቫይረሶች ስልታዊ ዳግም የቀኝ ግዛት እና ቁሳዊ ወንጌል ብዝባዞዎች ፣ያልተለመዱ እና ሥነምግባር የጎደለው ማንነቶች ለመደበኛነት ምንም መሠረት የሌለው መለያ በማውረስ የብዝሃነትና የብዝሃ-ተፈጥሮን ውበትን አጉዱፈዋል።
ከመላው የአለም ህዝብ አንድ ፐርሰንቱ የአለምን ሀብት፣ኢኮኖሚና ፖለቲካን ይቆጣጠራሉ። ቁሳዊነትና እራስ ወዳድነት ሰብአዊነትን በማበላሸት ስለራሶ ብቻ በማሰብ ስለራሶ ብቻ እንዲኖሩ ያመላክታሉ ።ስግብግብነት እና ማታለያዎች በግለሰብ ፣ በብሔራዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የተለመዱ ሆነዋል።የ 99% ህይወት በሁሉም ቦታ አሳዛኝ ነው! ድህነት በአሰቃቂ ሁኔታ ተስፋፍተዋል ፣የፍትሕ መጓደሎች በሚያስደነግጥ ሁኔታ በቂ ምንያት መሆን እና የሰዎች መፈናቀል ፣ስደተኞች እንደ የመፍራት እና የምእራቡ ውድቀት ምልክተወ ተደርገው መገለፅ ፣ ሁሉም ኢ-ሰብአዊ እና አድሎአዊ ተግባራት ትክክል መሆን ፣የስህተት ገለፃ በሽታን በዘር ስሞች መሰየም ፣ አፍሪካን የሙከራ እና የድህነት መኖሪያ ማድረግ ።
በእነዚህ ሁሉ መካከል COVID19 ከጥቂት ወራት በፊት ብቅ ብሏል ፣እናም የበላይ ኃይሎችን እየፈተነ ልዕለ ሀብት ፣ልዕለ ብልግናዎች ፣ልዕለ ሁሉነገሮች ፣ትእቢት ፣ድንቁርና ፣ ናርሲዝም ባጠቃላይ ለዚህ ተጋለጡ።
ኢኮኖሚያዊ ፣ ወታደራዊ ፣ፖለቲካዊ ግዙፍ ነን እያሉ ሱፎክሩ የነበሩ ለቲኒሽ እንስሳ በጉልበታቸው ተንበረከኩ ።(አዎ! ለቲኒኒሽ እንስሳ) ከግራና ቀኝ ፣ ከላይና ታች ፣ ከውጪና ከውስጥ እርዳታ ለማግኘት ችላ ያሉትን እና የረሱትን አንድ መንፈሳዊና ተፈጥሮያዊ ሃይል ልመና ላይ ይገኛሉ ። የነሱ ልዕለ ሁሉነገር ዋጋ ቢስ ሆነ ኮቪድ–19 በአጉሊ መነፅር በሚጋፈጡበት ጊዜ የአቧራ ሃይል እንጂ ሌላ ሆኖ አላገኙትም።የተከማቸው የኒኩለር እና ወታደራዊ ሃይላቸው እቺን ቲኒሽዬ ቫይረስ እንኳን መግደል ተሳነው ። እንዴት ያሉ የሀብት ብክለትና ሴይጣናዊ መሳሪያዎች ናቸው! ኮቪድ 19 ፍርኦናዊው አመለካከታቻው ሁነኛ ጥቃት ነው።
በእርግጥ ፣ COVID19 ዓለም አቀፋዊ የጤና ችግር እና አሳዛኝ እንደሆነ ሁሉ ካፒታሊዝም እና ሶሻሊዝም የተቀመጡ ስህተቶችን እና ጉዳቶችን ለማስተካከል እና ለማረም መጥቷል ፡፡ በዓለም ዙሪያ ተተግብሯል። እነዚህን ማህበራዊ፣ ቀውሶችን ለማስተካከል ፣ለማረም እና ለማከም ጊዜው ደርሷል ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሰው ሰራሽ ቫይረሶች ተፈጥሮን የተበላሹ የሰዎች ስርዓቶችን በመዋጋት ላይ ናቸው፡፡
19 ሰው ሰራሽ ኦርጋኒክ ያልሆኑ ኮሮናዎች
1,የወለድ ተመን
2, ድህነት
3,ጦርነቶች
4, የጦር መሳሪያዎች ንግድ
5,ፕሮፖጋንዳ
6,የአካባቢ ድንቁርናን ማበጀት
7, ረሃብ
8, የአልኮል መጠጥ
9, ሱሰኝነት
10,የውስጥ ብጥብጥ
11,ቁማር
12,የፋሽን ኢንዱስትሪ
13, የመዝናኛ እንዱስትሪ
14,የውጪ ሰው መጥላትና ዘረኝነት
15,አክራሪነት
16,አድሎና ፅንፈኝነት
17,ሰዎችን ማፈናቀል
18, ትእቢት እና ድንቁርና
19,ግብዝነት እና እራስን መካብ
እነዚህ ሰው ሰራሽ ኮሮናዎች በሰብአዊነት ላይ ጥቃጥ አድርሰዋል። 19 ሰው ሰራሽ ቫይረሶች በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ በሰው ልጅ ላይ በአለም ዙሪያ ችግር እያደረሱ ያሉት እነዚህ ናቸው ።እነዚህ ሰው ሰራሽ ሱናሚ ቫይረሶች የሚሊዮኖች ሞት መንስኤ ሆነዋል። እነዚህ 19 ሰው ሰራሽ ወረርሺኝ የካፒታሊስትና ፣የኮሚኒስት ፣አክራሪነት ፣ስግብግብነት እና እራስ ወዳድነትን መሰረት ያደረጉ የአስተዳደር መዋቅሮች ውጤቶች ናቸው። አስቸኳይ እርማት በቀጣይነት የሰውን ዘር ለመታደግ ትኩሩትን ይሻሉ።
ኮቪድ 19 የተሻለ ለውጥ ያመጣል ብለን ተስፋ እናድርግ ። ጊዜው የአርአያ ለውጥ ነው! ጊዜው እራሳችንን የምናሰደተካክልበት ፣የምናርምበት እና እራሳችንን የምንመራበት ነው!
ከ COVID19 ያገኘናቸው ትምህርቶች እቅድ እንዲኖራቸው ነው የቅድመ-COVID19 ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስህተቶችን ሁሉ በመዋቅራዊ ሁኔታ ማስተካከል ፡፡እድሳት በመውሰድ መታደስ! ሰብአዊነት ማስቀደም! የተፈጥሮ ሀብቶችን ለአለም አቀፍ ማመቻቸት፡፡ ከግለሰባዊ ጥቅም ይልቅ በማህበራዊ እና በጋራ ጥቅም ላይ ማቶከር።
አለማችን እድሳት ትሻለች አለም አቀፍ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ኖሮ አለም ወደ ቀድሞ ሰብአዊነት ስትመለስ የብዙዎችን ስቃይ ማዳን ትችላለች ።
ልዕለ ሁሉነገር ነን ባዮች እራሳቸውን አስተካክለው ወደ ልዕለ ሰብአዊነት ከተመለሱ የሁሉ ቫይረሶች ማጥፋት ይቻላል።ይህ ከሆነ ወደ አለም ስምምነት ፣ ብልጽግና ፣ ጤና እና ሰላም ጉዞ ማድረግ የሚቻል ነው ፣ Will የሚለው አባባል ካለ ፣ መንገድ አለ። ዓለም በልቡ ላይ ያሰፈረውን ጨለማ ሽፋን ማስወገድ ያለበት ጊዜው አሁን ነው።ብቸኛው መንገድ ይህ መለወጥ ብቻ ነው ። ኮቪድ –19 እንዳስተማረን መረዳዳታችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን። እኛ ካልተረዳዳን የማንረባ ለቲኒሽ ደቃቃ ቫይረስ ሰለባ በመጋለጥ የምንጠፋ ነን ።
የካፒታሊዝም እና የኮሚኒዝም መሪዎች አመለካከታቸውን ካስተካከሉ ፍትሃዊነት እና ሰብአዊነት ታድሰው ወደ ሰላም መመለስ ይቻላል ።
የተደራጀ የአስተዳደር ስርዓት እንፈልጋለን ፡፡ “ዜግነታችን ሰብአዊነት ነው” ፣ “አገራችን ምድር ናት” ፣ “ህገ-መንግስታችን መለኮታዊ ነው” እና ደራሲው “አንድ እና አንድ ፈጣሪ” ነው። እነዚህን በትክክል የምንከተል ከሆነ ለሰው ሰራሽ 19 ኮሮናዎች ክትባቶቻቸውን ይከፍትልናል ። ክትባቶቹ ፦
1,ፀሎት (ዱዓ)
2,ትህትና
3,መከባበር
4,ያለንን መካፈል
5, ፍቅር
6,ልግስና በጎ ፍቃደኝነት
7,ምህረት
8,ንሳሃ (ቶውባ)
9,ፆም
10,እኩልነት
11,ትክክለኛነት
12,ምስጋና
13,ይቅር ባይነት
14,እምነት
15,አንድነት
16,ትእግስት
17, ርህራሄ
18,እርጋታ
19,ሀይማኖተኛ
እነዚህ ክትባቶች ከወሰደን ወደ ሰላምና ብልፅግና ያደርሱናል ።
በመጨረሻም ፣ እንደ ስደተኛ ፣ የልማት ሰራተኛ ፣ ተመራማሪ ፣ የሙያ አሰልጣኝ እና ፕሮፌሰር ለምወዳት ሀገሬ ኢትዮጲያ የማስተላልፈው መልክት አለኝ ፦
እንደምታዩት ትልቅ ቁጥር ያለው ዜጎች በስደት ላይ የሚገኙት በሃይማኖት ግጭት ፣ በብሄር ጭቆና ፣ በአመራር አንባገነንነት ነው። ስለዚህ በፖሊታካ የበላይነይ አንዱ በሌላው ላይ ኮሮና መሆን የለበትም።ከ 80 በላይ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች መሐል ፍትህ ፣ እኩልነት እና ሰላም የሰዎች የአካል ክፍሎች ናቸው ፣ እናም እኛ የጋራ እሴቶቻችንና ባህላዊ (ወይም ልዩነት) ሰብአዊነታችንን ጠብቀን እንኑር ፡፡ እርስ በርሳችሁ በመከባበር።ይህን ከተገበርን እኛ እንደ ኢትዮጵያዊነታችን በሰላም ይሰማናል፡፡
በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የ19 ሰው ሠራሽ ኮሮናዎች ረዘም ያለ ሥሪት እና ዝርዝሮችን ለማንበብ ከፈለጉ ፣ እባክዎን የ IHMS የፌስቡክ ገፃችንን ይመልከቱ ፡፡
ለመላው የእስልም እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳን ፆም ምኞቴን እገልፃለሁ ።
በሌላ አስተምህሮት ቀጣይ እስክንገናኝ ወሰላም አሌይኩም!